Doesn't suit? No problem! You can return within 30 days
You won't go wrong with a gift voucher. The gift recipient can choose anything from our offer.
30-day return policy
ድህነት የገንዘብ እጥረት ሳይሆን አስተሳሰብ ነው። ብዙ ገንዘብ ኖሯቸው ከድህነት ግን ያልተላቀቁ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ምንም እንኳን የገንዘብ እጥረት ባይኖርባቸውም፣ አስተሳሰባቸው ውስጥ ያለው ድህነት ስላልተሸነፈ፣ ይህ፣ ድህነት ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት፣ በባህሪያቸው፣ በስብዕናቸው፣ በተለያየ መልኩ ይገለጣል። ስለዚህ፣ ድህነት የገንዘብ ድህነት ብቻ ሳይሆን፣ የባህሪ ድህነት፣ የአስተሳሰብ ድህነት፣ የስብዕና ድህነት፣ የግንኙነት ድህነት፣ የባህል ድህነት ወ.ዘ.ተ ተብሎ ሊዘረዘር ይችላል። ከእነዚህ ሁሉ ግን፣ መሰረታዊው የአስተሳሰብ ድህነት ነው።
አስተሳሰባችን ውስጥ ድህነት ካለ በኢኮኖሚ አቅማችን እንኳን እጥረት ባይኖርብን፣ ከድህነት ተጽዕኖ ውጭ ግን አይደለንም። ድህነትን ከአስተሳሰባቸው ማስወገድ የቻሉ ከኢኮኖሚያቸው ድህነትን ማስወገድ ያን ያህል ከባድ አይሆንባቸውም። ምክንያትይም የኢኮኖሚ ድህነትም ቢሆን መነሻ መሰረቱ የአስተሳሰብ ድህነት ነው። በዚህ መጽሐፍ የግል ገንዘብ (personal finance) አጠቃቀምንና ከገንዘብ ጋር የተያያዘ አስተሳሰብን በተመለከተ ስነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ መርሆች ተጣምረው ቀርበዋል።
Hi! I'm Libroamiko, your book advisor.
How can I help you?